የሲኖዶሱ 55ኛ መደበኛ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ስብሰባ በሰላም ተጠናቀቀ። The meeting was successfully concluded in peace.
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ደቡብ ምዕራብ ቤቴል ሲኖዶስ 55ኛ መደበኛ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ስብሰባውን አካሄደ፡፡በዚህም ስብሰባ ላይ በርካታ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለ18ኛ መደበኛ የሲኖዶሱ ካውንስል መርቷል።ካውንስሉም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያጸደቀ ሲሆን ከእነዚህ ውሳኔዎች መካከል የሲኖዶሱ ወንጌልና ቲዮሎጊ መምሪያ ዳይሬክተርና የቻርለስ ሀስፕልስ ሴሚኔሪ ፕሪንሲፓል ምርጫ ዋነኞቹ ናቸው።
በመሆኑም ካውንስሉ በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ ለቀጣይ አራት ዓመታት እንዲያገለግሉ፦
- ቄስ ጌታሁን ጌሽ፡ የሲኖዶሱ ወንጌልና ቲዮሎጊ መምሪያ ዳይረክተር፤
- ቄስ አለማዬሁ ጊሲ፡ የቻርለስ ሀስፕልስ ሴሚናሪ ፕርንሲፓል አድርጎ መርጧል።
በዚህም ስብሰባው በሰላም መጠናቀቁ ታውቋል።
EECMY South West Bethel Synod Holds 55th Executive Board Meeting
The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus (EECMY) South West Bethel Synod held its 55th Regular Executive Board Meeting, passing key decisions and leading to the 18th Regular Synod Council.
The Council elected the following leaders for the next four years:
- Rev. Getahun Gesh – Director, Gospel & Theology Department
- Rev. Alemayehu Gisi – Principal, Charles H. Haspels Seminary
The meeting was successfully concluded in peace.












