Uncategorized
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ደቡብ ምዕራብ ቤቴለተ ሲኖዶስ የክርስቲያን ሴቶች አገልግሎት ክፍል በስሩ ለሚገኙ የፕሪስቤተሪዎች ክርስቲያን ሴቶች አገልግሎት ኮሚቴዎች ስልጠና ሰጥቷል::

የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ቄስ ማርቆስ ማይትን ስልጠናውን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት “የክርስቲያን ሰቶች አገልግሎት የቤተክርስቲያኒቱ አንዱ አገልግሎት ዘርፍ ነው፡፡ በመሆኑም ሴቶች እግዚአብሔር የሰጣቸውን ጸጋ ተጠቅመው ለወንጌል እና ለማህበራዊ አገልግሎት እንዲጠቀሙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡” ብለዋል፡፡
ሰልጠናውም በቤተክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ የሴቶች ሚና በሚል ሃሳብ የተሰጠ ነው ሲሉ የአገልግሎት ክፍሉ አስተባባሪ ቄስ ትዕግስት ዮናስ ተናግረዋል፡፡











